November 8, 2019

“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል.. ” (ዮሐ. 14፡ 25-26)።

መንፈስ ቅዱስ በኛ ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ ቃሉን ማስተማር ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ የቃሉን ፍቺ ለአማኞች ያበራል። ጌታችንከላይበሰፈረውክፍል ይንንኑ አስተምሮናል። ስለዚህ ጉዳይ ሐዋሪያው ዮሐንስ ሲጽፍ “እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እን...

November 1, 2019

የእግዚአብሔር ቃል የጌታን እራት ስንወሰድ ለጌታ መታሰቢያ እንድናደርገው ያስተምረናል። ለመሆኑ የጌታን እራት ስንወስድ የምናስበው ምንድን ነው? አንደኛ በጌታ የተደረገልንን እናስባለን። ይህም ማለት ስለ እኛ ደህንነት የተቆረሰልንን የጌታን ስጋ እና የፈሰሰልንን የጌታን ደም እናስባለን። እንጀራውን ቆርሰን ስንወስድ የስጋው መቆረስ ምሳሌ ነው። ጽዋውንም ቀድተን ስንጠጣ የደሙ መፍሰስ ምሳሌ ነው። ይህ ደግሞ ለተካፈልነው ሕይወት መሰረት ነው። ጌታ ኢየሱስ በቃሉ እንዳለ የጌታን ስጋ የበላ ደሙንም ደግሞ የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው። ከርሱ...

October 26, 2019

ከቤተ ክርስቲያናችን ራዕይ መካከል አንዱ “በእምነት ጠንካራ፣ በአእምሮ ደግሞ የላቁ ልጆችን ማሳደግ” ነው። ልጆቻችን በእምነት የጠነከሩ ሆነው እንዲያድጉ መትጋት አለብን። የዚህ ትጋት አቅጣጫ ደግሞ ልጆቻችን እግዚአብሔርን በግል እንዲያውቁና እንዲወዱ መርዳት ነው። ለዚህ ቁልፉ ነገር አዘውትረን ለልጆቻችን መጸለይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማርና ከቅዱሳን ልጆች ጋር ሕብረት እንዲኖራቸው ማመቻቸት ነው። እንዲሁም ልጆቻችን በእውቀትና በጥበብ ልቀት እንዲኖራቸው መቅረጽ ይገባናል።

እግዚአብሔር ቃሉን ለልጆቻችን እንድናስተምር አዟል።...

October 19, 2019

የእግዚአብሔር ፍቅር በልባቸን የፈሰሰው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው። በሮሜ 5:5 ላይ የእግዚአብሔር ቃል “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም” ይለናል። “ፈሰሰ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ፍቅር ያለገደብ ወደ እኛ እንደመጣ የሚገለጽ ነው። ለኛ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ወደር የለውም። የዚህን ፍቅር ጥልቀት ለመግለጽ ሐዋሪያው ጳውሎስ “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል” (ሮሜ 5:8) ይለናል። የእ...

October 11, 2019

“... መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ...” (ሐዋ. 1:8)

መንፈስ ቅዱስ የኃይል መንፈስ ስለሆነ በመንፈስ ቅዱስ ስንሞላ ኃይልን እንቀበላለን። መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን ኃይል በተለያየ መንገድ የሚገለጥ ነው። በላይ በሰፈረው ክፍል ቃሉ መንፈስ ቅዱስ በኛ ላይ ሲወርድ ኃይልን እንደምንቀበል ይናገራል። አያይዞም ደግሞ ይህ የሚሰጠን ኃይል ምስክሮች እንደሚያደርገን ይናገራል። መንፈስ ቅዱስ ከተሞላን በኋላ የጌታ ምስክሮች እንደምንሆን ይናገራል። ሁለት ነገሮች በዚህ ክፍል እንመለከታለን። በመጀመሪያ መንፈ...

October 4, 2019

“ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።” (ዮሐ. 7:37-39)

ባለፈው ሳምንት እንዳየነው መንፈስ ቅሱስ የጌታ ኢየሱስን ማንነትና አዳኝነት ይመሰክራል። በዛሬው መልዕክት ደግሞ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ የክርስቶስ ትንሳኤ ምስክር እንደሆነ እንመለከታለን። ጌታ ኢየሱስ በላይ የሰፈረው...

September 28, 2019

“ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል::” (ዮሐ. 15:26)

ይህ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ዘመን ነው። መንፈስ ቅዱስ አሁን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሆኖ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራል። መንፈስ ቅሱስ የጌታ ኢየሱስን ማንነት ይመሰክራል፤ የጌታ ኢየሱስን ትንሳኤ ይመሰክራል፣ የጌታን አዳኝነት ይመሰክራል። ያለ መንፈስ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ መመስከር አይቻልም። ለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ ለአገልግሎት ከመውጣታቸው በፊት መንፈስ ቅዱ...

September 21, 2019

ባለፈው ሳምንት በነበረን ኮንፈራንስ ላይ እግዚአብሔር “ይህ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ የስራ ዘመን” እንደሆነ ተናግሮናል። መንፈሳችንንም በዚህ ዙሪያ ሲያነቃቃው ነበር። እውነት ነው ይህ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ዘመን ነው። አሁን ከቤተ ከርስቲያን ጋር ሆኖ አብና ወልድን እያከበረ ያለው መንፈስ ቅዱስ ነው። ጌታ ኢየሱስ የምድር አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ አባቱ ከመሄዱ በፊት ለደቀመዛሙርቱ የሰጣቸው ትልቁ ተስፋ መንፈስ ቅዱስ ነው። ጌታ እንዲህ አላቸው፡ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አ...

September 15, 2019

እንደ አባቶች ፈለግ እንደ ሐዋሪያት፣

በፊቱ እንደ ተጉት በአንድ ልብ ጸሎት፣

የመንፈስን ሙላት እንደ ተቀበሉት፣

በግልጽ እንደ ናኙት የወንጌሉን ብስራት፣

በኃይል እንደ ሮጡት ለገባቸው እውነት፣

እንዳለቆማቸው ሰይፍና እስራት፣

እንደ ገሰገሱት በአላማ ጽናት፣

እኛም ስንጋጠም ስንቆም በሕብረት፣
ልዩነት ደብዝዞ ሲፈካ አንድነት፣
ለአምላክ ደስ የሚያሰኝ የሚያውድ መስዋዕት፣

በመንፈስ ተሳስረን ስናቀርብ በውበት፣

ሽታችን ይወጣል ይማርካል ነፍሳት።
ከራስ እንደ ’ሚወርድ እንደ አሮን ዘይት፣

ይገለጣል በኛ የክርስቶስ ሕይወት፣
ጨለማን የሚገፍ የብርሃን ፍካት።

እኛ...

September 6, 2019

ሰው ተስፋ ያደረግውን ማንኛውንም ነገር የመጠበቅ ዝንባሌ አለው።መጠበቅ በራሱ ክፋት የለውም።በሌላ መልኩ በእጅ ያለውን፣የተያዘውን መጠበቅ ወይንም መንከባከብም ተገቢ ነው። ቀጠሮ የተቆረጠለትን፤ቀንና ሰአት የተወሰነለትን ነገር መጠበቅም መጥፎም አይደለም።ነገር ግን በመጠበቅ ውስጥ መዘግየት አለ።የሁኔታዎች መዘግየት ደግሞ ዝለት፤ዝንጉንትን፤ቁጣንና ተስፋ መቁረጥን ይወለዳል።መጠባብቅ ውስጥ ግን መታደስ ፤መዘጋጀት፤ ተስፌኛንትና መበርታት አሉት። እነዚህም የመጠባበቅ መለያ ባሂሪያቶቹ ናችው።

በሉቃስ ወንጌል መዕራፍ 15:25-32 ጠፍቶ ስለተግኘ...

Please reload

Recent Posts

September 15, 2019

Please reload

Archive
Please reload

Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Google+ Basic Square

 

4455 N Seeley Ave

Chicago, Il 60625

1:30PM TO 4:00PM SUNDAY

7:00PM TO 9:00PM FRIDAY

 

Get it on iTunes
Screen Shot 2019-05-10 at 6.36.24 PM.png
  • Facebook Social Icon
  • Twitter Social Icon
  • Google+ Social Icon
  • YouTube Social  Icon