February 14, 2020

በመዝሙር 23 ንጉስ ዳዊት እግዚአብሔር በጠላቶቹ ፊት ለፊት ገበታን በፊቱ እንዳዘጋጀለት ይዘምራል። ገበታ ሁለት ነገሮችን ያመለክታል። አንደኛ ገበታ መክበርን ማሳያ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የወዳጅነት መገለጫ ነው። በዚህ ስፍራ ዳዊት እግዚአብሔርን ትልቅ ግብዣ እንዳዘጋጀና ወዳጁን እንደጋበዙ አስተናጋጅ ያስበዋል። እንደሚታወቀው ገበታ የሚዘጋጀው ድግስ ሲኖር ነው:: ድግስ ደግሞ የሚኖረው አንድም የከበረን እንግዳ ለማስተናገድ ነው ወይንም ደግሞ የከበረ በዓልን ለመዘከር ነው። በዚህ ክፍል ግን የምናየው ገበታ የተዘጋጀው የነገስታት ንጉስ፤ የ...

July 5, 2019

ፍቅር ጥልቅ ነገር ነው። ፍቅር አያስገድድም ነገር ግን ብርቱ ገፊ ነው። ከያኒያን ዜማን ከግጥም አዋህደው፤ ቀለም በቡርሽ አጣቅሰው፤ ድርሰት ከምናብ አፍልቀውና ምስል ከድምጽ አቀናብረው ስለ ፍቅር ጥልቀት፣ ጥንካሬና ውበት ይቀኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስም የፍቅርን ኃይል ሲገልጽ “ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና ... ብዙ ውኃ ፍቅርን ያጠፋት ዘንድ አይችልም” ይላል። (መኃ 8፡ 6-7) እግዚአብሔርም ሰውን የወደደበት ፍቅር እጅግ ብርቱና ጥልቅ ነው። እግዚአብሔር አንድ ልጁን ለመስቀል ሞት አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ ሰውን ሁሉ ወዷል። መጽሐፍ ቅ...

May 25, 2019

“ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።” (ዕብ. 11፡ 6)

አባታችን ሄኖክ በትውልዱ መካከል ለየት ያለ ሰው እንደነበረ መጽሐፍ ያስተምረናል።የትውልዶችን የዘር ሃረግ የያዘውን ዘፍጥረት ምዕራፍ ሰድስትን ስናነብ የብዙ አባቶች ህይወት የተዘገበው“እገሌ ይህን ያህል አመት ኖረ፣ ወንድኖችና ሴቶች ልጆችን ወለደ፣ ሞተም” እየተባለ ነው። ነገር ግን ሄኖክ ላይ ስንደርስ አተራረኩ ለየት ይላል። ስለ ሄኖክ ሲናገር “ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔ...

January 26, 2019

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር
እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል።” ዮሐ. 14፡15-16

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ አባቱ ከመሄዱ በፊት አንድ
ታላቅ ተስፋ ሰጥቶናል። ጌታ እርሱ ከሄደ በኋላ ሌላ አጽናኝ እንደሚመጣልን ተናግሮን ነበር። ህይ
“ሌላ አጽናኝ” የተባለው መንፈስ ቅዱስ ነው። እርሱ እንደ ኢየሱስ ያለ ሌላ አጽናኝ ነው። “ሌላ”
የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን በተጻፈበት በክሪክ ቋንቋ “allŏs” ማለት ሲሆን ትርጉ ደግም “another
of the exact, i...

January 19, 2019

ጌርጌሴኖን በሚባል ከተማ የሚኖር አንድ በአጋንት እስራት ውስጥ የነበረ ሰውን ታሪክ በማርቆስ
5 ላይ እናነባለን። ይህ ሰው በታላቅ ስቃይ ውስጥ ነበር። የሚኖረው ከሰው ተለይቶ በመቃብር ስፍራ
ነበር። በሰንሰለትና በእግር ብረት ሊታሰር አልቻለም። በውስጡ ባለው አጋንታዊ ኃይል የታሰረበትን
ሰንሰለት ይበጥሳል፤ የእግር ብረቱንም ይሰባብራል። ስለዚም ማንም ሰው የማይቀርበው ኃይለኛ ነበር።
ይህም ብቻ ሳይሆን በርሱ ያለው አጋንንት ሌትና ቀን ያስጮኸው ነበር። ሰውነቱንም በድንጋይ ይጭር
ነበር።
ይህ በዚህ ታላቅ እስራት የነበረ ሰው ጌታ ወደዚ...

January 12, 2019

በፈለገ-አብርሃም ለጥሪው ልታዘዝ፣
በስራ ሚገለጥ የምነትን ፅድቅ ልያዝ፣

በመንፈሱ እንዳየ ከሞተ ኣካል ህይወት፣

ያስነሳዋል እንዲል ልጅ አቅርቦ መስዋኢት፣

እኔም ድልን ላብስር ትንሳኤውን ላሽትት።

የልብ ብርህን ስጠኝ እንደ ባርያህ ሙሴ፣

ከግብፅ ተድላ ይልቅ እንድትሻህ ነፍሴ፣

ለም ዝና ሚያስንቅ ክብርህን አይቼ፣

ጉልበቴ ሳይደክም ሳይፈዙ አይኖቼ፣

በከፍታ ልሙት ተራራ ወጥቼ።

እግሬ ዘይት ይጥለቅ በአሴር ምሳሌ፣

እድሜዬም ሲጨምር እንዲታደስ ሃይሌ፣

ይሞላ ጏዳዬ በሚተርፍ በረከት፣
ቀባኝ በመንፈስህ አጫማኝ በብረት፣

ጠላቶቼን ላድቅቅ በስምህ ሃይል ጉልበት።

ታ...

December 14, 2018

“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ።” (1 ጴጥ. 2፡9)

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን “እግዚአብሔር እርሱ ብረሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም።” (1ዮሐ. 1፡5) ብርሃን የሕወት፣ የተስፋ፣ የእውቀት፣ የጽድቅ... ወዘተ ምልክት ነው። ጨለማ ደግም የሞት፣ የተስፋ መቁረጥ፣ የድንቁርና፣ የሃጢያት... ወዘተ ምልክት ነው። እግዚአብሔር ባለበት ሁሉ ያለው ሕይወት ነው፣ ተስፋ ነው፣ ጽድቅ ነው፣ መገለጥ ነ...

December 8, 2018

“ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።” (መዝ. 50፡23)

ምስጋና እግዚአብሔርን የምናከብርበት መንገድ ነው። ምስጋናችን በፊቱ እንደሚያርግ መስዋዕት ለእግዚአብሔር የመአዛ ሽታ ነው። በምስጋና ውስጥ ደግሞ የደህንነት መንገድ አለ። እግዚአብሔርን ምስጋናን ለሚሰዋ ማዳኑን፣ ምህረቱን፣ እርዳታውን ይለግሳል። ምስጋና ዘርፈ ብዙ ነው፤ በዋናነት ግን ስናመሰግን ሶስት ነገሮችን አንዳደርጋለን።

(1) ስናመሰግን እግዚአብሔር ላደረገልን ነገር እውቅና እየሰጠን ነው፦ እግዚአብሔር ከቁጥር በላይ የሆ...

November 24, 2018

መዝሙር 107 የምስጋና መዝሙር ነው። ዘማሪው እግዚአብሔር ለእስራኤል ያደረገውን እየቆጠረ እዝቡ አምላካቸውን እንዲያመሰግኑ ይጋብዛል። መዝሙሩ የሚጀምረው “ሃሌ ሉያ” በሚል የሃሴት ምስጋና ነው። “ሃሌ ሉያ” የሚለው ቃል “ሃሌል” እና “ያህ” የሚሉ የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን የመጀመሪያው ቃል በደስታ፣ የለገደብ፣ በሙሉ ኃይል ማመስገን የሚለውን ሃሳብ ይይዛል። ሁለተኛው ቃል “ያህ” ደግሞ “ያህዌ” የሚለውን የእግዚአብሔርን ስም የሚወክል ነው። እንግዲህ “ሃሌ ሉያ” ስንል እግዚብሔርን በደስታ፣ በሙሉ ኃይልና መለቀቅ አመስግኑ የሚል የአ...

November 3, 2018

“...ሥራህ ምንድር ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ ወዴት ነው? ወይስ ከማን ወገን ነህ? አሉት። እርሱም፦ እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ አላቸው።” (ዮናስ 1፡8-9)

ብዙ ሰው ስራህ ምንድን ነው ተብሎ ሲጠየቅ “እኔ መሃንዲስ ነኝ”፤ “እኔ ሃኪም ነኝ”፤ “እኔ ሼፍ ነኝ” ወይንም እንዲህና እንዲያ ነኝ ብሎ ይመልሳል። ይህ ጥያቄ ለነብዩ ዮናስ አንድ ጊዜ ቀርቦለት ነበር። በትንቢተ ዮናስ ላይ እንደምናነበው ዮናስ እግዚአብሔር ወደ ነነዌ ሊልከው ወዶ ሳለ እርሱ ግን ከእግዚአብሔር...

Please reload

Recent Posts

March 20, 2020

Please reload

Archive
Please reload

Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Google+ Basic Square