March 20, 2020

“ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።” (ሉቃ. 24:5)

የክርስትናችን መሰረቱ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ስለተነሳ ነው ከማይጠፋ ዘር ሁለተኛ የተወለድነው እና የማያልፍ ርስት የተጠበቀልን። (1ጴጥ. 1:3-5) ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ስለተነሳ ነው የትንሳኤ ተስፋ ያለን። (1ቆሮ. 15:20) ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተነሳ ነው የሞትና የሲዖል ኃይል የተሻረው። (ሮሜ 6:9) ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ስለተነሳ ነው ዳቢሎስ ድል የተነሳው። (ቆላ. 2:15) እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተነሳ ነው መንፈስ ቅዱስ ወደ...

March 13, 2020

የእግዚአብሔር እረኝነት በምድር በሚኖረን ሕይወት በሚገለጠው የእርሱ መግቦት፣ ጥበቃ፣ መሪነትና ባርኮት ብቻ የሚገለጥ ሳይሆን የዘላለምን ተስፋ የሚሰጥ ነው። ለዚህ ነው ዳዊት በመዝሙር 23 መደምደሚያ ላይ “በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ” በማለት የዘመረው። ጌታችንም እርሱ እውነተኛ የበጎች እረኛ እንደሆነ አስተምሮ “እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም” በማለት ከርሱ ጋር ለዘላለም በሕይወት እንደምንኖር የጸና የተስፋ ቃል ሰጥቶናል (ዮሐ. 10:28)።

መጽሐፍ ቅዱሳችን ይህን...

March 7, 2020

ንጉስ ዳዊት በተደጋጋሚ በዝማሬው ከሚያነሳቸው ሃሳቦች መካከል የእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት ዋንኞቹ ናቸው። በመዝሙር 23 ላይም የእግዚአብሔር ቸርነትና ምሕረት በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እንደሚከተሉት በእምነት ያውጃል። ዳዊት በእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት ይታመናል። በመዝሙር 6:4 ላይ “አቤቱ ... ስለ ቸርነትህም አድነኝ” እያለ ይጸልያል። በመዝሙር 26:6 ላይ ደግሞ “አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥ ከጥንት ጀምሮ ናቸውና” በማለት ይማጸናል። በመዝሙር 51:1 ላይ ደግሞ “አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም...

February 29, 2020

ንጉስ ዳዊት በመዝሙር 23 ከእግዚአብሔር እረኝነት ጋር አያይዞ እግዚአብሔር የተትረፈረፈን ሕይወት የሚሰጥ አምላክ እንደሆነ ይቀኛል። ይህንን ሃሳብ የሚገልጸው “ጽዋዬም የተረፈ ነው” በማለት ነው። በዚህ ስፍራ አግባብ “ጽዋዬ” በማለት ዳዊት የሚገልጸው ከእግዚአብሔር የተቀበለውን በረከትና ሕይወት ነው። በሌላም ስፍራ እግዚአብሔር እድል ፋንታው መሆኑን በመግለጽ “እግዚአብሔር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣዬንም የምታጠና አንተ ነህ” በማለት ያመሰግናል (መዝ. 16:5)። እግዚአብሔር ለዳዊት የሰጠው ጽዋ የሞላ ብቻ ሳይሆን ሞልቶ...

February 22, 2020

መዝሙረኛው ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ስለሆነ እራሴን በዘይት ቀባኝ በማለት ይዘመራል። ዳዊት በተደጋጋሚ በእግዚአብሔር የተቀባ ሰው ነው። ገና በብላቴናነቱ እግዚአብሔር ሳዖልን የእስራኤል ንጉስ እንዳይሆን ከናቀው በኋላ ሳሙኤልን ቀንዱን በዘይት ሞልቶ ወደ እሰይ ቤት እንዲሄድ አዘዘው። ሳሙኤል ዘለግ ያሉትን የእሰይን ልጆች ሊቀባ ወዶ ነበር እግዚአብሔር ግን ሰው እንደሚያይ አያይምና ከሰባቱም የእሰይ ልጆች የሚቀባው አልተገኘም ነበር። ዳዊት የቀረ ልጅ የለም ወይ ተብሎ ተፈልጎ ከእረኝንቱ ስፍራ ተጠርቶ ተቀባ (1 ሳሙ. 16:13)። በመቀ...

February 7, 2020

ሰሞኑን በተከታታይ እያየን እንዳለነው እግዚአብሔር እረኛችን ነው -- ይመግበናል፤ እግዚአብሔር እረኛችን ነው -- ይመራናል፤ እንዲሁም ከኛጋርያለውእግዚአብሔርየሞትን ኃይል ስለሻረው በሞት ጥላ መካከል ብናልፍ እንኳ ክፉን አንፈራም። ዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር እረኛችን ጠባቂያችን እንደሆነ እንመለከታለን። የእግዚአብሔር እረኝነት ከሚገለጥበት አስደናቂ መንገድ አንዱ ጥበቃው ነው።

እውነተኛ እረኛ ለበጎቹ እራሱን ያኖራል። ጌታ ኢየሱስ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር “መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራ...

January 31, 2020

በዚህ ክፍል ዳዊት ሞት እንደማያስፈራው ይዘምራል። በመሰረቱ ሞት በክርስቶስ የመስቀል ስራ አምኖ ከእግዚአብሔር ጋር ላልታረቀ ሰው አስፈሪ ነው። በጌታ ያልሆነ ሰው ምንም ጀግና ቢሆን ከሞት ጋር ሲፋጠጥ ይፈራል። ለዚህ ነው አጋግ የተባለው የአማሌቅ ንጉስ ሳሙኤል ፊት ሲቀርብ “በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?” ያለው (1 ሳሙ. 15:32)። በክርስቶስ የሆንን ቅዱሳን ግን ከሞት ፍርሃት ነጻ ወጥተናል።

ሞት አስፈሪ የማይሆነው የመውጊያ ኃይሉ ሲወሰድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን የሞት መውጊያ ኃጢያት ነው። ሞት በኃጢያት አማካኝነ...

January 24, 2020

የእግዚአብሔር እረኝነት ከሚገለጥበት መንገድ አንዱ መሪነቱ ነው። እረኛ በጎቹን እንደሚመራቸው ሁሉ ጌታም ይመራናል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን ስለ እውነተኛ እረኛ ሲናገር በመጀምሪያ እውነተኛ እረኛ መለያው የእርሱ የሆኑት በጎች ድምጹን ለይተው ያውቁታል፤ ደግሞም ይሰሙታል (ዮሐ. 10:3-4)። በጎቹ የእረኛቸውን ድምጽ ከለሌላ ድምጽ ጋር አያምታቱም። ይህ እንግዲህ የሚሆነው በበጎቹና በእረኛው መካከል ተግባቦትና ትውውቅ እንዲሁም በመቀራራብ የተወለደ መታመን ስላለ ነው። እረኛው ለበጎቹ ድምጹን ካሰማ በኋላ በስማቸው ጠርቶ ይ...

January 18, 2020

የእግዚአብሔር እረኝነት ከሚገለጥበት መንገድ አንዱ የእርሱመጋቦት ነው። እግዚአብሔር እረኛችን ስለሆነ ይመግበናል። በመዝሙር 23 ዳዊት የእግዚአብሔርን መጋቢነት ሲገልጽ እግዚአብሔር በለመለመ መስክ እንደሚያሳድረውና በእረፍትም ውሃ ዘንድ እንደሚመራው በመተማመን ያውጃል። ይህ መተማመን የመጣው የእግዚአብሔርን መልካም እረኝነት ተለማምዶ ከመወቅ ነው።

በጎች ለመኖር ምግብና ውሃ ያስፈልጋቸዋል። ስለዚህም መልካም የሆነ እረኛ የሚያደርገው አንዱ ነገር በጎቹ እንዳይራቡና እንዳይጠሙ ግጦሽ ባለበት የለመለመ መስክ ያሰማራቸዋል። እንዲሁም በልተው ደ...

January 10, 2020

ባለፈው ሳምንት እንዳየነው መዝሙር 23 እግዚአብሔር የሕዝቡ እረኛ እንደሆነ ያስተምረናል። ከዚህም ተነስተን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር እረኝነት የሚያስተምረንን ሃሳቦች በጥቂቱ አይተናል። በተጨማሪም ዳዊት የራሱን ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን የግል ልምምድ መሰረት አድርጎ እግዚአብሔር ለእርሱ በግሉ እረኛው እደሆነ በመረዳትይህንን መዝሙር እንደዘመረተመልክተናል። ዛሬደግም “የሚያሳጣኝምየለም” የሚለውን ሃሳብ እናያለን።

ዳዊት እግዚአብሔር እረኛው ስለሆነ የሚያሳጣው ነገር እንደሌለ ያውጃል። “የሚያሳጣኝም የለም” በሚለው ክፍል...

Please reload

Recent Posts

March 20, 2020

Please reload

Archive
Please reload

Follow Us