“በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን?
(2ቆሮ 13፡5)
እንኳን ጌታ ለ2018 ዓመተ ምህረት ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ። ቀናት ቀናትን
ወልደው አሮጌ አመት አልፎ በአዲስ አመት ሲተካ በቸርነቱ አመትን የሚያቀዳጀውን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። (መዝ. 65፡11) እያንዳንዱ አመት ከርሱ የምንቀበለው ጸጋና በረከት ነው። ዘመንን፣ እድሜን የሚሰጥ እርሱ ነው። ካሌብ ሕይወቱን ዞር ብሎ ተመልክቶ “እነዚህን አርባ አምስት ዓመት...