December 6, 2019

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል።”

ዮሐ. 14፡15-16

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ አባቱ ከመሄዱ በፊት አንድ ታላቅ ተስፋ ሰጥቶናል። ጌታ እርሱ ከሄደ በኋላ ሌላ አጽናኝ እንደሚመጣልን ተናግሮን ነበር። ህይ “ሌላ አጽናኝ” የተባለው መንፈስ ቅዱስ ነው። እርሱ እንደ ኢየሱስ ያለ ሌላ አጽናኝ ነው። “ሌላ” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን በተጻፈበት በክሪክ ቋንቋ “allŏs” ማለት ሲሆን ትርጉ ደግም “anotheroftheexact,identi...

November 29, 2019

“እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል።” (ዮሐ. 16:8) መንፈስ ቅዱስ አሁን ሶስት ወሳኝ ስራዎች ያደርጋል። አንደኛ ስለ ኃጢያት አለምን

ይወቅሳል። ሁለተኛ የክርስቶስን ጽድቅ ለአለም ይገልጻል። ሶስተኛ ስለ የመጨረሻውን ፍርድ ያስጠነቅቃል። በዚህ ክፍል እንደምናየው በኃጢያት እና በፍርድ መካከል የክርስቶስ ጽድቅ መካከለኛ ሆኖ አለ። ኃጢያት ወደ ፍርድ ይወስዳል ነገር ግን ከፍርድ መውጫው መንገድ የክርስቶስን ጽድቅ መቀበል ብቻ ነው።

መንፈስ ቅዱስ አለምን ስለ ኃጢያት ይወቅሳል። ይህም ሰው ኃጢያተኝንቱን...

November 22, 2019

“መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም፥ የምድርንም ፊት ታድሳለህ።” (መዝ. 104:30)

መጽሐፍ ቅዱስ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሲያስተዋውቀን እርሱ ከአብና ከወልድ ጋር በመፍጠር ስራ ላይ ነበር። በፍጥረት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ “በውኃ ላይ ሰፍፎ” ነበር። መንፈስ ቅዱስ ባዶ ለነበረች፣ አንዳችም ላልነበረባት፣ በጨለማ ለነበረች ምድር ሙላት፣ ቅርጽ፣ ብርሃንና ውበት ሲያበጅ እናያለን። ስለዚም መዝሙረኛው “መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም፥ የምድርንም ፊት ታድሳለህ” በማለት ተቀኝቷል (መዝ. 104:30)። መንፈስ ቅዱስ ለሰማያት ውበትን የሰጠ እ...

November 15, 2019

“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ... እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል” (ዮሐ. 14፡26)።

መንፈስ ቅዱስ ግሩም አስተማሪ ነው። መንፈስ ቅዱስ በአብ ውስጥ ያለውን ስለሚያውቅ የጠለቀውን የቃሉን ፍቺ ያበራልናል። እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ቅዱስ የቃሉ ደራሲ ስለሆነ በቃሉ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ኃሳብ ለቅዱሳን ያሳውቃል። ስለዚህም ወደ መንፈስ ቅዱስ የበለጠ ስንቀርብ እግዚአብሔርን የበለጠ እያወቅን እንሄዳለን። መንፈስ ቅዱስ የቃሉ አስተማሪ ብቻ ሳይሆን ቃሉንም የሚያሳስብ መንፈስ ነው።

መንፈስ ቅዱስ...

November 8, 2019

“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል.. ” (ዮሐ. 14፡ 25-26)።

መንፈስ ቅዱስ በኛ ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ ቃሉን ማስተማር ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ የቃሉን ፍቺ ለአማኞች ያበራል። ጌታችንከላይበሰፈረውክፍል ይንንኑ አስተምሮናል። ስለዚህ ጉዳይ ሐዋሪያው ዮሐንስ ሲጽፍ “እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እን...

November 1, 2019

የእግዚአብሔር ቃል የጌታን እራት ስንወሰድ ለጌታ መታሰቢያ እንድናደርገው ያስተምረናል። ለመሆኑ የጌታን እራት ስንወስድ የምናስበው ምንድን ነው? አንደኛ በጌታ የተደረገልንን እናስባለን። ይህም ማለት ስለ እኛ ደህንነት የተቆረሰልንን የጌታን ስጋ እና የፈሰሰልንን የጌታን ደም እናስባለን። እንጀራውን ቆርሰን ስንወስድ የስጋው መቆረስ ምሳሌ ነው። ጽዋውንም ቀድተን ስንጠጣ የደሙ መፍሰስ ምሳሌ ነው። ይህ ደግሞ ለተካፈልነው ሕይወት መሰረት ነው። ጌታ ኢየሱስ በቃሉ እንዳለ የጌታን ስጋ የበላ ደሙንም ደግሞ የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው። ከርሱ...

October 26, 2019

ከቤተ ክርስቲያናችን ራዕይ መካከል አንዱ “በእምነት ጠንካራ፣ በአእምሮ ደግሞ የላቁ ልጆችን ማሳደግ” ነው። ልጆቻችን በእምነት የጠነከሩ ሆነው እንዲያድጉ መትጋት አለብን። የዚህ ትጋት አቅጣጫ ደግሞ ልጆቻችን እግዚአብሔርን በግል እንዲያውቁና እንዲወዱ መርዳት ነው። ለዚህ ቁልፉ ነገር አዘውትረን ለልጆቻችን መጸለይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማርና ከቅዱሳን ልጆች ጋር ሕብረት እንዲኖራቸው ማመቻቸት ነው። እንዲሁም ልጆቻችን በእውቀትና በጥበብ ልቀት እንዲኖራቸው መቅረጽ ይገባናል።

እግዚአብሔር ቃሉን ለልጆቻችን እንድናስተምር አዟል።...

October 19, 2019

የእግዚአብሔር ፍቅር በልባቸን የፈሰሰው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው። በሮሜ 5:5 ላይ የእግዚአብሔር ቃል “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም” ይለናል። “ፈሰሰ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ፍቅር ያለገደብ ወደ እኛ እንደመጣ የሚገለጽ ነው። ለኛ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ወደር የለውም። የዚህን ፍቅር ጥልቀት ለመግለጽ ሐዋሪያው ጳውሎስ “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል” (ሮሜ 5:8) ይለናል። የእ...

October 11, 2019

“... መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ...” (ሐዋ. 1:8)

መንፈስ ቅዱስ የኃይል መንፈስ ስለሆነ በመንፈስ ቅዱስ ስንሞላ ኃይልን እንቀበላለን። መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን ኃይል በተለያየ መንገድ የሚገለጥ ነው። በላይ በሰፈረው ክፍል ቃሉ መንፈስ ቅዱስ በኛ ላይ ሲወርድ ኃይልን እንደምንቀበል ይናገራል። አያይዞም ደግሞ ይህ የሚሰጠን ኃይል ምስክሮች እንደሚያደርገን ይናገራል። መንፈስ ቅዱስ ከተሞላን በኋላ የጌታ ምስክሮች እንደምንሆን ይናገራል። ሁለት ነገሮች በዚህ ክፍል እንመለከታለን። በመጀመሪያ መንፈ...

October 4, 2019

“ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።” (ዮሐ. 7:37-39)

ባለፈው ሳምንት እንዳየነው መንፈስ ቅሱስ የጌታ ኢየሱስን ማንነትና አዳኝነት ይመሰክራል። በዛሬው መልዕክት ደግሞ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ የክርስቶስ ትንሳኤ ምስክር እንደሆነ እንመለከታለን። ጌታ ኢየሱስ በላይ የሰፈረው...

Please reload

Recent Posts
Please reload

Archive
Please reload

Follow Us
  • Facebook Basic Square
  • Google+ Basic Square